የቤተሰብ አስፈላጊነት፡
በአንድ ሀገር ጠንካራ ቤተሰብ ሲኖር፥ ጠንካራ ማሕበረሰብ እንዲፈጠር አስተዋጽኦ ይኖረዋል። ምክኒያቱም፣ ማህበረሰብ የቤተሰብ ስብስብ ነውና። ስለዚህ ጠንካራ ቤተሰብ ሲኖር፥ ማሕበረሰቡም እየተጠናከረ ይሄዳል ማህበረሰብ እየተጠናከረ ሲሄድ ደግሞ ሀገርን መስርቶ ጠንካራ ሀገር የመፍጠር ብቃት ይኖረዋል። ስለሆነም፥ ቤተሰብ የሕብረተሰብ ብሎም የሐገሪቱ መሰረት ነው። ቢባል የሚጋነን አይሆንም። ምክኒያቱም፥ ከፍ ሲል ለመግለጽ እንደተሞከረው፣ በማሕበረሰቡ ውስጥ የሚገኘው እያንድአንዱ ቤተሰብ ጠንካራና የተደራጀ […]